የለውዝ ወይም ኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞዎች
************************** ******
ውልደቱን ደቡብ አሜሪካ ያደረገውን ለውዝ በየቀኑ የአንድ እጆን እፍኝ ያህል የመብላት ልምድ ካሎት የሚከተሉትን የጤና በረከቶች ያፍሳሉ፡፡
1. ከፍተኛ ኃይል ያላብሰናል፡- ለውዝ በኃይል የተሞላ ነው (ከ100 ግራም ለውዝ 567 ካሎሪን ማግኘት ይቻላል)
2. የደም ቅባት ወይም ኮሌስትሮል መጠንን ያስተካክላል፡፡ በኦሊክ ሲድ የበለጸገ ስለሆነ የደም ቅባትን ጤናማ ከማድረጉ ባሻገር ኮሮናሪ አርተሪ የተባለውን ለልብ በሽታ የሚያጋልጥ ሕመምን ያስወግዳል፡፡
3. ከፍተኛ ፕሮቲን ያለው ሲሆን አራቺንና ኮን አራቺን የተባሉት ፕሮቲኖች ለሰውነት ግንባታና ዕድገት ወሳኝ ናቸው፡፡
4. የጨጓራ ካንሰርን ይከላከላል፡- ምክንያቱም ለውዝ በውስጡ ፀረ-ካንሰር ንጥረነገሮችን በብዛት ይዟል፡፡
5. የነርቭ፣የልብ፣የመርሳት በሽታዎችን የመከላከል ብቃቱ የሚደነቅ ሲሆን ለበሽታ አምጪ ሕዋሳት ለሆኑት ቫይረስና ፈንገሶች ጠላት ነው፡፡
6. በጭንቅላት ውስጥ የሚገኙ ቧንቧዎች ጥበትን በመከላከል ስትሮክ በተባለ በሽታ እንዳንጠቃ ይከላከላል፡፡ የደም ቧንቧን የሚሰፉ ሆርሞኖች በብዛት እንዲመነጩ ያደርጋል፡፡
7. አስፈላጊ ቫይታሚን ቢ-ኮምፕሌክ የሆኑትን ሪቦፍላቪን፣ኒያሲን፣ቲያሲን፣ፓናቶኒክ አሲድ፣ቫይታሚን ቢ-6 እና ፎላትስ ይዟል፡፡
8. የሀሞት ጠጠር እንዳይፈጠር ይከላከላል፡- የሀሞት ጠጠር በደም ቅባት ወይም በኮሌስትሮል የሚመጣ ሲሆን ለውዝ ደግሞ የደም ቅባትን በመቆጣጠር ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች የሀሞት ጠጠር እንዳይፈጠር ይከላከልላቸዋል፡፡
9. በማዕድናት የበለፀገ በመሆኑ በውስጡ ኮፐር፣ ማንጋኒዝ፣ ፖታስየም፣ ካልስየም፣ ብረት፣ ማግኒዚየም ዚንክና ሲሊኒየም ይዟል፡፡
10. ክብደት የመቀነስ ውጥን ካሎት ለውዝ መብላት አንዱ የልምዶ አካል ያድርጉት፡፡
ልብ ይበሉ፡- ሁሌም ቢሆን የሚበሉት ለውዝ ያልሻገተና ያልተበላሸ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ የሻገተ ለውዝ አፍላተቶክሲን የተባለ ካንሰር ሊያመጣ የሚችል ንጥረ ነገር በውስጡ ስለሚፈጥር ለበሽታ ሊያጋልጦት ይችላል፡፡ ይሁንና ጤናማ ለውዝ የሚበሉ ከሆነ ከላይ የቀረቡትን የጤና በረከቶች ያገኛሉ፡፡
እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!
ምስጋናችን ከልብ ነው!
**************************

No comments:
Post a Comment