Information Technology Kilil

“Information science is the science and practice dealing with the effective collection, storage, retrieval, and use of information. It is concerned with recordable information and knowledge, and the technologies and related services that facilitate their management and use.

Responsive Ads Here

Tuesday, February 11, 2020

የለውዝ ወይም ኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞዎች

የለውዝ ወይም ኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞዎች
********************************
ውልደቱን ደቡብ አሜሪካ ያደረገውን ለውዝ በየቀኑ የአንድ እጆን እፍኝ ያህል የመብላት ልምድ ካሎት የሚከተሉትን የጤና በረከቶች ያፍሳሉ፡፡

1. ከፍተኛ ኃይል ያላብሰናል፡- ለውዝ በኃይል የተሞላ ነው (ከ100 ግራም ለውዝ 567 ካሎሪን ማግኘት ይቻላል)

2. የደም ቅባት ወይም ኮሌስትሮል መጠንን ያስተካክላል፡፡ በኦሊክ ሲድ የበለጸገ ስለሆነ የደም ቅባትን ጤናማ ከማድረጉ ባሻገር ኮሮናሪ አርተሪ የተባለውን ለልብ በሽታ የሚያጋልጥ ሕመምን ያስወግዳል፡፡

3. ከፍተኛ ፕሮቲን ያለው ሲሆን አራቺንና ኮን አራቺን የተባሉት ፕሮቲኖች ለሰውነት ግንባታና ዕድገት ወሳኝ ናቸው፡፡

4. የጨጓራ ካንሰርን ይከላከላል፡- ምክንያቱም ለውዝ በውስጡ ፀረ-ካንሰር ንጥረነገሮችን በብዛት ይዟል፡፡

5. የነርቭ፣የልብ፣የመርሳት በሽታዎችን የመከላከል ብቃቱ የሚደነቅ ሲሆን ለበሽታ አምጪ ሕዋሳት ለሆኑት ቫይረስና ፈንገሶች ጠላት ነው፡፡

6. በጭንቅላት ውስጥ የሚገኙ ቧንቧዎች ጥበትን በመከላከል ስትሮክ በተባለ በሽታ እንዳንጠቃ ይከላከላል፡፡ የደም ቧንቧን የሚሰፉ ሆርሞኖች በብዛት እንዲመነጩ ያደርጋል፡፡

7. አስፈላጊ ቫይታሚን ቢ-ኮምፕሌክ የሆኑትን ሪቦፍላቪን፣ኒያሲን፣ቲያሲን፣ፓናቶኒክ አሲድ፣ቫይታሚን ቢ-6 እና ፎላትስ ይዟል፡፡

8. የሀሞት ጠጠር እንዳይፈጠር ይከላከላል፡- የሀሞት ጠጠር በደም ቅባት ወይም በኮሌስትሮል የሚመጣ ሲሆን ለውዝ ደግሞ የደም ቅባትን በመቆጣጠር ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች የሀሞት ጠጠር እንዳይፈጠር ይከላከልላቸዋል፡፡

9. በማዕድናት የበለፀገ በመሆኑ በውስጡ ኮፐር፣ ማንጋኒዝ፣ ፖታስየም፣ ካልስየም፣ ብረት፣ ማግኒዚየም ዚንክና ሲሊኒየም ይዟል፡፡

10. ክብደት የመቀነስ ውጥን ካሎት ለውዝ መብላት አንዱ የልምዶ አካል ያድርጉት፡፡



ልብ ይበሉ፡- ሁሌም ቢሆን የሚበሉት ለውዝ ያልሻገተና ያልተበላሸ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ የሻገተ ለውዝ አፍላተቶክሲን የተባለ ካንሰር ሊያመጣ የሚችል ንጥረ ነገር በውስጡ ስለሚፈጥር ለበሽታ ሊያጋልጦት ይችላል፡፡ ይሁንና ጤናማ ለውዝ የሚበሉ ከሆነ ከላይ የቀረቡትን የጤና በረከቶች ያገኛሉ፡፡




እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!


《ማድረግ የሌለብዎ ነገር》

《ማድረግ የሌለብዎ ነገር》 --------------~------------- ... ☞ የባትሪ ቻርጅ በጣም ሎው ሲሆን፣ ወይም ሲቀንስ (20% በታች) ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ፡፡ ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው የጨረር መጠን ይጨምራል። ... ☞ ሞባይል ተጠቃሚ ከሆኑ ሲነጋገሩ ወደ ጆሮዎ እና ጭንቅላትዎ እጅግ በጣም አያስጠጉ ፡፡ ከቻሉ ቢያንስ ከ5 ሳንቲ ሜትር በላይ ራቅ በማድረግ ኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲየሽን ከተባለው አደገኛ ጨረር ራስዎን ይጠብቁ፡፡ ... ☞ የሞባይል ስልኮን # ታቅፈው አይተኙ፡፡ በእንቅልፍ ወቅት ባትሪውን ያጥፉ ወይም ከአልጋዎ 1.8 ሜትር በማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው ኤሌክትሮማግኔትክ ራስዎን በተቻለ መጠን አያጋልጡ፡፡ ... ☞ ነፍሰጡር እናቶች ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ፡፡ የጽንሱ ሕዋሳት ለኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽን እጅግ በጣም አለርጂክ ናቸው፡፡ ስለዚህ አቀማመጡንም ሆነ አጠቃቀሙን ከጽንሱ ራቅ ባለ ሥፍራ ይሁን፡፡ አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ አለበዎት፡፡ ... ☞ ብረት ነክ ነገሮች ባሉበት ሥፍራ ሞባይል መጠቀም አያዘውትሩ፡፡ ብረት የኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽኑን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል፡፡ ስለዚህ መኪና ውስጥ፣ አውሮፕላን ውስጥ፣ ሊፍት ውስጥ፣ ባቡር ውስጥ፣ ብረት አጥር ወይም በር አካባቢ፣ የብረታብረት ወርክሾፕ ውስጥ፣ ጋራዥ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ፡፡ የሚጠቀሙም ከሆነ ለአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን፡፡ ... ☞ በተለይ! በተለይ!!! ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ወጣት ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይሻላል፡ ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎቻቸውን እጅግ በጣም ይጎዳዋል፤ ለካንሰርም ያጋልጣቸዋል፡፡ ... ☞ በበለጸጉት አገሮች ከ15 ዓመት በታች ባሉ ልጆች ውስጥ ለሚከሰተው ሞት በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክንያት የጭንቅላት እጢ ነው፡፡ ወላጆች ይህንን እውነታ በመገንዘብ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ሞባይል መጠቀምን በመደበኛነት ልጆች አዘውትረው እንዳይለምዱት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ... ☞ አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑት ሁሉ የጭንቅላታቸው ራስ ቅል በጣም ስስ ነው፡፡ ስለዚህ ጨረሩ ሙሉ ለሙሉ በስሱ አጥንት በኩል ወደ አንጎላቸው ሰርፆ ስለሚገባ ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ ... ☞ ጨቅላ ሕፃናትና ትናንሽ ልጆች አጠገብ ሁነው ሞባይል አዘውትረው የሚነጋገሩ ከሆነ ለአደጋ ስለሚያጋልጣቸው አጠቃቀሙንና አቀማመጡ ከእነርሱ ራቅ ባለ ሁኔታ ላይ ያድርጉት፡፡ ☞ እባክዎ! ሌሎች መረጃዎች እንዲደርስዎ ከፈለጉ ገጹን #like እና መረጃው ለጓደኞችዎ እንዲድርስ ከፈለጉ #share ያድርጉ።

Monday, February 10, 2020

የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?

💻የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡
➢ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን። ይሁን እንጂ አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::
❖ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል ....
☛ሼር በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎችም ይትረፉ፡፡
❒የ F1 ጥቅሞች
► ከ”Windows ቁልፍ (button) ጋር በጋራ ስንነካው help menuን ያመጣልናል፡፡
► Excel እና Word በምንጠቀምበት ወቅት ከ Control ጋር በጋራ ስንነካው Hides or displays ribbon menu ያደርግልናል፡፡
❒የ F2 ጥቅሞች
◕ Alt + Ctrl + F2 - opens Document Library in Microsoft Office
◕ Allows you to edit the selected folder or file name in Windows Explorer
❒የ F3 ጥቅሞች
► Opens search feature in Windows Explorer
► Shift + F3 - lets you change from lowercase to uppercase to all caps in Word
► Opens find feature in Firefox and Chrome
❒የ F4 ጥቅሞች
◕ Alt + F4 closes window
◕ Places the cursor in the address bar in Explorer
❒የ F5 ጥቅሞች
► Starts slideshow in Power Point
► Refreshes Internet browser pages
► Opens Find and Replace in Microsoft Office
❒የ F6 ጥቅሞች
◕ Goes to the next page in a split screen in Microsoft Word
◕ Ctrl + F6 lets you easily switch between Word documents
❒የ F7 ጥቅሞች
► Alt + F7 does a spelling and grammar check in Microsoft Word
► Shift + F7 open Thesaurus in Microsoft Word
❒የ F8 ጥቅሞች
◕ In Excel, enables extend mode for arrow keys
◕ Enables safe mode in Windows
❒የ F9 ጥቅሞች
► Ctrl + F9 inserts empty fields into Word
► Updates fields in Word
❒የ F10 ጥቅሞች
◕ Opens menu bar
◕ Ctrl + F10 maximizes window in Word
◕ Shift + F10 does the same thing as a right click
❒የ F11 ጥቅሞች
► Exits and enter full screen mode in browsers
► Shift + F11 adds a new spreadsheet in Excel
❒የ F12 ጥቅሞች
◕ Opens Save As in Word
◕ Shift + F12 saves Word document
◕ Ctrl + F12 opens Word document


የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት መንከባከቢያ ውጤቶች

የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት በሚል ውድ የውበት መጠበቂያና የፀጉር
መንከባከቢያ ውጤቶችን ከመሸመት ይልቅ በቀላሉ የምናገኛቸውን ነገሮች እና ተፈጥሯዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለፀጉራችን እንክብካቤ ማድረጉ የሚመረጥ ሲሆን፥ የውበት ባለሙያዎችም ይህንኑ እንድናደርግ ነው የሚመክሩን።
በመሆኑም እነዚህን አምስት አማራጮች እንድንተገብራቸው ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ያወጣው መረጃ ይመክራል።
1.ዘይት መጠቀም፣
የወይራ ዘይት፣ የኮኮናት ዘይት አልያም ሌላ ማንኛውንም አይነት ዘይት ወስደን እናፈላዋለን፤ ከዚያም ለብ ሲል በጥንቃቄ የፀጉራችንን ስር በደንብ እያዳረስን እንቀባዋለን፤ ለአንድ ሰዓት ያህልም በሻሽ ወይም ፎጣ ጠቅልለን ካቆየን በኋላ በሻምፖ እንለቃለቀዋለን።
2. ተፈጥሯዊ ጭማቂዎች (ጂውሶችን) መጠቀም፣
አመሻሽ ላይ የነጭ፣ ቀይ ሽንኩርት አልያም የዝንጅብል ጭማቂን ወስደን በተመሳሳይ የፀጉራችን ስሩን በደንብ መቀባት፤ ከዚያም በማግስቱ ልንለቃለቀው እንችላለን።
3. የጭንቅላት ማሳጅ (መታሸት)
የፀጉራችን ስር አካባቢ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በየቀኑ የምናደርገው የማሸት (ማሳጅ) የማድረግ ተግባር የደም ዝውውርን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ የደም ዝውውር መቀላጠፍም በአንፃሩ የፀጉር ሴሎችን እድገት ያነቃቃል።
4.አረንጓዴ ሻይ መጠቀም፣
ሁለት የአረንጓዴ ሻይ ከረጢት በአንድ ኩባያ የፈላ ውሃ ላይ በመጠቀም የፀጉራችንን የስረኛው ክፍል መቀባት፣ ለአንድ ሰዓት ያህል ካቆየነው በኋላም እንደምንፈልገው ልንለቃለቀው እንችላለን።
በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የምናገኘው አንቲኦክሲዳንትስ የፀጉር መነቃቀልን ይከላከላል።
በተጨማሪም የፀጉር ዕድገትን ያፋጥናል።
5. ጭንቀትን ማስወገድ፣
ለፀጉር መሳሳት እና መነቃቀል አብይ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ጭንቀት ነው።
በመሆኑም ከአላስፈላጊ ጭንቀት ራስን መከላከል እና የተመስጦ (ሜዲቴሽን) ተግባርን በማከናወን የፀጉር መነቃቀልንም ሆነ መሳሳትን መከላከል ይቻላል።

short story

📚ደስ የሚል አጠር ያለ አስተማሪ ታሪክ
👉ሰውዬው አስር ክፍል ቤት ሰርቶ ብቻውን ሲኖር አንድ ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ጌታ ነው።
"ወይ አምላኬ ጌታዬ አንተ እኔ ቤቴ መጣህ?"ብሎ በ
ደስታ ተቀብሎት አንድ ክፍል ቤት ሰጥቶት መኖር ጀመሩ።
በሌላኛው ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ሰይጣን ነው። ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል ?" አለው።
👉ሰውዬውም ተሰምቶት ሁለት ክፍል ቤት ለጌታ ጨምሮለት እርሱ ሰባት ክፍል ይዞ መኖር ቀጠሉ።
አሁንም በሚቀጥለው ቀን በሩተንኳኳ ሲከፍት ሰይጣኑ ነው።
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል?" አለው ጌታም " ቤቱ ያንተ እንጂ የእኔ አይደለም" አለው።
👉ሰውዬውም በጣም ተሰማውና ከጌታ ጋር እኩል ለእኩል ተካፈሉ ። ነገር ግን ቤቱ ከቀድሞ ይልቅ ተንኳኳ።
አዝኖም ይዘጋና ጌታዬ ሆይ አለው።
ጌታም ቤቱ ያንተ እንጂ የእኔ አይደለም አለው።በዚህ ጊዜ
👉ሰወዬው ለራሱ አንድ ክፍል ቤት ይዞ ዘጠኙን ክፍል ቤት ለጌታ ሰጠው ። ነገር ግን ከቀድሞወ ይልቅ በጣም ተንኳኳ ።ሲከፍት ሰይጣን ነው።
በሩን ይዘጋና ወደ ጌታ ሄደ"ጌታዬ ሆይ ምሥጢሩምንድነው ?
ጌታም የቀድሞውን መልስ ሰጠው።
በዚህ ጊዜ አስሩን ክፍል ለጌታ አስረከበው።
ጌታም አንድ ክፍል ቤት ለሰውዬው ሰጠው።
በሚቀጥለው ቀን በሩ ተንኳኳ ።ጌታም ሊከፋት ተነሳ ሲከፍት ሰይጣን ነው። ሰይጣንም "ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወኩም ነበር "ብሎ ሄደ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ መንኳኳት ቆመ።
ሁሉንም የህይወታችን ክፍል ለፈጣሪያችን ካላስረከብን መንኳኳቱ አይቀርም።
10% ስንሰጥ ይንኳኳል 30% ስንሰጥ ይንኳኳል 50% ስንሰጥ ይንኳኳል 90% ስንሰጥ ይንኳኳል 100% ስንሰጥ ግን በራችን መንኳኳቱ ይቆማል እኛ በራችንን ከከፈትን ሰይጣን ይፈታተነናል ነገር ግን ጌታ ሲከፍትጰ ግን ሰይጣን አንገቱን ደፍቶ ተመልሶ ይሄዳል ።
ጌታ ሰማይን የደስታ ሀገር ያድርጋት ሙሉ በሙሉ የፈጣሪ ፍቃድ የፀናባት በመሆኗ ነው። ባንተም ህይወት የሰማይ ደስታ የሚመጣው የፈጣሪ ፍቃድ በህይወትህ ሙሉ በሙሉ ሲፈፀም ነው።
ስለዚህ ፈጣሪን እረኛህ አድርገው።
በፍፁም ልብህ ተከተለው የሚያስፈልጉህን ነገሮችም አንተን ይከተሉሃል ።
🌹"ሙሉ ህይወታችን ለእግዚአብሔር እንስጥ
እናስረክበው።"

short story

🌀🌀ልብ ብለው ያንብቡ!! 🌀🌀
❀━┅┉┈በድጋሚ ┈┉┅━❀
ልጁ ነገውን ሚስት ሊያገባ ሽር ጉድ ላይ ሳለ እናት ድንገት ከዚህ አለም በሞት ትለየውና የሰርጉን ፕሮግራም ወደ አመት አዘዋወረው ። የማይደርስ የለምና ያ የቀጠሮ ቀን አመቱን አክብሮ ብቅ አለ ። ልጁም የሚፈልጋትን ሴት አገባ ። ያን ግዜ አባት በባዶ ቤት ብቻቸውን ሊቀሩ ተገደዱ ።

ምክንያቱም ባለቤታቸው ከሞተች በኋላ ከዚህ አንድ ልጃቸው ሌላ ማንም አልነበራቸውም ። ልጅም ከአዲሷ ሚስቱ ኑሮ ጀመረ ። ልጁ አንዳንዴ ሚስቱን ይዟት አባቱን ሊጠይቅ ይመጣል ። አንዳንዴ ደሞ እሱ አባቱን ጠይቆ እስኪመለስ እሷ ቤተሰቦቿ ዘንድ ትጠብቀዋለች ። ብዙ ግዜ የሷን ቤተሰቦች ብቻ እንዲጠይቅ ታስገድደው ነበር ።

በዚህ መልኩ አምስት አመታት ተቆጠሩ ። በዚህ መሀከል እኚህን ምስኪን አባት በእርጅና ላይ በሽታው አዳከማቸው ። የአባቱ ሁኔታ ያሳሰበውም ልጅ አባቱን ቤት ሊወስዳቸው እና ሙሉ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ሲጠይቃቸው ። የልጁ ሚስቱ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው እንግዳ እንዳይሆኑ ስለስጉ ጥያቄውን አልተቀበሉትም ። ከዚያም የረጅም ግዜ የልጃቸው ውትወታ ለጥያቄው እጅ እንዲሰጡ አደረጋቸውና ልጃቸው ቤት ቀሪ ዘመናቸውን ሊያጠናቅቁ ብቅ አሉ ።

ያን ግዜ የልጃቸው ሚስት ደስታ ራቃት ። ሁለት አይነት ምግብ ማብሰል ጀመረች ለሽማግሌው በግዴለሽነት ትሰራና ታቀርብላቸው ነበር ። አባት ምግብ ብቻቸውን መብላት ቢከብዳቸው እንኳን ከልጃቸውና ከልጅ ልጆቻቸው አብረው መብላት አትፈቅድላቸውም ነበር ። የሚስቱ እና ያባቱ ሁኔታ ትንግርት የሆነበትም ልጅ በሁለት መዕበላት ውስጥ ሆኖ ይናወጥ ጀመር ከአባቴ ልሁን ወይስ ከሚስቴ !!!

ያን ግዜ ሚስት እንድ ሀሳብ ሰነዘረች ፦"ለምን ሚስት አናመጣላቸውም እነሱንም ትንከባከባለች እኛም እንገላገላለን" አለች ። ልጅም በዚህ እድሜያቸው አግብተው መኖር እንደማይችሉ ስላመነ አንድ አማራጭ ፊቱ ላይ ድቅን አለለት ። አረጋውያን ማቆያ/ሰው የሌላቸው ሽማግሌዎች የሚኖሩበት ድርጅት ውስጥ ሊወስዷቸው ወሰኑ እና ይዘዋቸው ሄዱ ። ልጁም ለዘመናት አብሮት የኖረውን የገዛ አባቱን በገዛ እጁ ገብቶ ማያውቅበት ግቢ ውስጥ አስገብቶት እንባውን እያፈሰሰ ተመለሰ ።

አባቱን እዛ ግቢ ውስጥ ካስገባቸው በኋላ በሳምንቱ ሊጠይቃቸው ወደ ግቢው ሲገባ አባት በብጣሽ ወረቀት መልዕክት አስቀምጠውለት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል ። መልዕክቱ እንዲህ ይል ነበር ፦

"ልጄ !!! ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ ድሮ ከስራ ስገባ አንተ ያለህበት ክፍል ገብቼ ላንተ መጫወቻዎችን ጣፋጭ ነገሮችን ስሰጥህ ነበር ።

ልጄ !!! ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ ዋና ላስለምድህ ገንዳ ውስጥ አንተን ተሸክሜ ምዋኝበት ግዜ ነበር።

ልጄ !!! ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ አንተ ህፃን እያለህ ቢሮ ይዤህ ስሄድ አንተም ቢሮ ውስጥ የሚጠቅሙኝን ወረቀቶች ስትቀዳድድብኝ በፍቅር ፈገግ እያልኩ የምመለከትህ ግዜ ነበር ።

ልጄ !!! በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ምርጥ ግዜያት ሁሉ ደስ የሚለኝ ላንተ የምትፈልገውን ሁሉ ልብስ ልገዛ በኪሴ ያለውን ብር ባጠቃላይ ሳወጣ እና አንተ አምሮብህ እኔ ደሞ የተቀደደ ልብስ ስለብስ ነበር ።

ልጄ አሁን እኔ አንተን አልወቅስህም ። ነገር ግን በእንባ ተሞልቼ ይሄን ምፅፍልህ የኔ መጨረሻ እንዲህ ይሆናል ብዬ አስቤ ስለማላውቅ ነው ። የህይወቴ መጨረሻ ባንተ እቅፍ እንዲሆን ነበር ምኞቴ ። ውድ አባትህ" እንብቦ እንደጨረሰ እንባውን እያፈሰሰ ፀፀቱን ተሸክሞ ወጣ ።
___________________________________________
በህይወት እስካላችሁ ድረስ አባታችሁን እናታችሁን እያገለገላችሁ ኑሩ ። ""ቆም ብለክ አስብ አስቢ ።


👉🏿 ፌስቡክን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡

💁🏾💁🏾✍🏿👉🏿 ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከው መጣጥፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ካገኘኅው አንተም ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ ሼር ያድርጉላቸው።
___________________
ሼር አድርጉ እባካችሁን መልካም ቀን

የለውዝ ወይም ኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞዎች

የለውዝ ወይም ኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞዎች ************************** ****** ውልደቱን ደቡብ አሜሪካ ያደረገውን ለውዝ በየቀኑ የአንድ እጆን እፍኝ ያህል የመብላት ልምድ ካሎት የሚከተሉትን የጤና በረከቶች ያ...