Information Technology Kilil

“Information science is the science and practice dealing with the effective collection, storage, retrieval, and use of information. It is concerned with recordable information and knowledge, and the technologies and related services that facilitate their management and use.

Responsive Ads Here

Monday, February 10, 2020

short story

📚ደስ የሚል አጠር ያለ አስተማሪ ታሪክ
👉ሰውዬው አስር ክፍል ቤት ሰርቶ ብቻውን ሲኖር አንድ ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ጌታ ነው።
"ወይ አምላኬ ጌታዬ አንተ እኔ ቤቴ መጣህ?"ብሎ በ
ደስታ ተቀብሎት አንድ ክፍል ቤት ሰጥቶት መኖር ጀመሩ።
በሌላኛው ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ሰይጣን ነው። ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል ?" አለው።
👉ሰውዬውም ተሰምቶት ሁለት ክፍል ቤት ለጌታ ጨምሮለት እርሱ ሰባት ክፍል ይዞ መኖር ቀጠሉ።
አሁንም በሚቀጥለው ቀን በሩተንኳኳ ሲከፍት ሰይጣኑ ነው።
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል?" አለው ጌታም " ቤቱ ያንተ እንጂ የእኔ አይደለም" አለው።
👉ሰውዬውም በጣም ተሰማውና ከጌታ ጋር እኩል ለእኩል ተካፈሉ ። ነገር ግን ቤቱ ከቀድሞ ይልቅ ተንኳኳ።
አዝኖም ይዘጋና ጌታዬ ሆይ አለው።
ጌታም ቤቱ ያንተ እንጂ የእኔ አይደለም አለው።በዚህ ጊዜ
👉ሰወዬው ለራሱ አንድ ክፍል ቤት ይዞ ዘጠኙን ክፍል ቤት ለጌታ ሰጠው ። ነገር ግን ከቀድሞወ ይልቅ በጣም ተንኳኳ ።ሲከፍት ሰይጣን ነው።
በሩን ይዘጋና ወደ ጌታ ሄደ"ጌታዬ ሆይ ምሥጢሩምንድነው ?
ጌታም የቀድሞውን መልስ ሰጠው።
በዚህ ጊዜ አስሩን ክፍል ለጌታ አስረከበው።
ጌታም አንድ ክፍል ቤት ለሰውዬው ሰጠው።
በሚቀጥለው ቀን በሩ ተንኳኳ ።ጌታም ሊከፋት ተነሳ ሲከፍት ሰይጣን ነው። ሰይጣንም "ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወኩም ነበር "ብሎ ሄደ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ መንኳኳት ቆመ።
ሁሉንም የህይወታችን ክፍል ለፈጣሪያችን ካላስረከብን መንኳኳቱ አይቀርም።
10% ስንሰጥ ይንኳኳል 30% ስንሰጥ ይንኳኳል 50% ስንሰጥ ይንኳኳል 90% ስንሰጥ ይንኳኳል 100% ስንሰጥ ግን በራችን መንኳኳቱ ይቆማል እኛ በራችንን ከከፈትን ሰይጣን ይፈታተነናል ነገር ግን ጌታ ሲከፍትጰ ግን ሰይጣን አንገቱን ደፍቶ ተመልሶ ይሄዳል ።
ጌታ ሰማይን የደስታ ሀገር ያድርጋት ሙሉ በሙሉ የፈጣሪ ፍቃድ የፀናባት በመሆኗ ነው። ባንተም ህይወት የሰማይ ደስታ የሚመጣው የፈጣሪ ፍቃድ በህይወትህ ሙሉ በሙሉ ሲፈፀም ነው።
ስለዚህ ፈጣሪን እረኛህ አድርገው።
በፍፁም ልብህ ተከተለው የሚያስፈልጉህን ነገሮችም አንተን ይከተሉሃል ።
🌹"ሙሉ ህይወታችን ለእግዚአብሔር እንስጥ
እናስረክበው።"

No comments:

Post a Comment

የለውዝ ወይም ኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞዎች

የለውዝ ወይም ኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞዎች ************************** ****** ውልደቱን ደቡብ አሜሪካ ያደረገውን ለውዝ በየቀኑ የአንድ እጆን እፍኝ ያህል የመብላት ልምድ ካሎት የሚከተሉትን የጤና በረከቶች ያ...