Information Technology Kilil

“Information science is the science and practice dealing with the effective collection, storage, retrieval, and use of information. It is concerned with recordable information and knowledge, and the technologies and related services that facilitate their management and use.

Responsive Ads Here

Monday, February 10, 2020

የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት መንከባከቢያ ውጤቶች

የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት በሚል ውድ የውበት መጠበቂያና የፀጉር
መንከባከቢያ ውጤቶችን ከመሸመት ይልቅ በቀላሉ የምናገኛቸውን ነገሮች እና ተፈጥሯዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለፀጉራችን እንክብካቤ ማድረጉ የሚመረጥ ሲሆን፥ የውበት ባለሙያዎችም ይህንኑ እንድናደርግ ነው የሚመክሩን።
በመሆኑም እነዚህን አምስት አማራጮች እንድንተገብራቸው ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ያወጣው መረጃ ይመክራል።
1.ዘይት መጠቀም፣
የወይራ ዘይት፣ የኮኮናት ዘይት አልያም ሌላ ማንኛውንም አይነት ዘይት ወስደን እናፈላዋለን፤ ከዚያም ለብ ሲል በጥንቃቄ የፀጉራችንን ስር በደንብ እያዳረስን እንቀባዋለን፤ ለአንድ ሰዓት ያህልም በሻሽ ወይም ፎጣ ጠቅልለን ካቆየን በኋላ በሻምፖ እንለቃለቀዋለን።
2. ተፈጥሯዊ ጭማቂዎች (ጂውሶችን) መጠቀም፣
አመሻሽ ላይ የነጭ፣ ቀይ ሽንኩርት አልያም የዝንጅብል ጭማቂን ወስደን በተመሳሳይ የፀጉራችን ስሩን በደንብ መቀባት፤ ከዚያም በማግስቱ ልንለቃለቀው እንችላለን።
3. የጭንቅላት ማሳጅ (መታሸት)
የፀጉራችን ስር አካባቢ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በየቀኑ የምናደርገው የማሸት (ማሳጅ) የማድረግ ተግባር የደም ዝውውርን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ የደም ዝውውር መቀላጠፍም በአንፃሩ የፀጉር ሴሎችን እድገት ያነቃቃል።
4.አረንጓዴ ሻይ መጠቀም፣
ሁለት የአረንጓዴ ሻይ ከረጢት በአንድ ኩባያ የፈላ ውሃ ላይ በመጠቀም የፀጉራችንን የስረኛው ክፍል መቀባት፣ ለአንድ ሰዓት ያህል ካቆየነው በኋላም እንደምንፈልገው ልንለቃለቀው እንችላለን።
በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የምናገኘው አንቲኦክሲዳንትስ የፀጉር መነቃቀልን ይከላከላል።
በተጨማሪም የፀጉር ዕድገትን ያፋጥናል።
5. ጭንቀትን ማስወገድ፣
ለፀጉር መሳሳት እና መነቃቀል አብይ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ጭንቀት ነው።
በመሆኑም ከአላስፈላጊ ጭንቀት ራስን መከላከል እና የተመስጦ (ሜዲቴሽን) ተግባርን በማከናወን የፀጉር መነቃቀልንም ሆነ መሳሳትን መከላከል ይቻላል።

No comments:

Post a Comment

የለውዝ ወይም ኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞዎች

የለውዝ ወይም ኦቾሎኒ የጤና ጥቅሞዎች ************************** ****** ውልደቱን ደቡብ አሜሪካ ያደረገውን ለውዝ በየቀኑ የአንድ እጆን እፍኝ ያህል የመብላት ልምድ ካሎት የሚከተሉትን የጤና በረከቶች ያ...